ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
114

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2017 በጀት አመት በዞኑ  ለሚገኙት መምሪያዎች  አገልግሎት የሚውሉ  የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በግለጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ  መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እና ሌሎች የእጅ መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4  ቋሚ እቃዎች /ፈርኒቸር/ እና ሎት 5 የመኪና ጎማዎች ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-

የግብር ከፋይ  መለያ ቁጥር /ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያላቸው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ  ብር/ እና በላይ ከሆነ   የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ  ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ  ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከአንድ ነጥብ አምስት ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ወይም ሥርዝ ካለም ፓራፍ ተደርጎ ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ 2/03/2017 እስከ 16/03/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና  ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1  በቀን 17/03/2017 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ  በ4፡30 ይከፈታል፡፡

አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ከላይ በሎቶ ከ1-5 በተገለፁት መሰረት የተዘረዘሩትን ግዥዎች የሚያቀርበው ለሰ/ጎ/ዞን ባሉት  ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡

የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

መሥሪያ ቤቱ  ይህንን ጨረታ ከላይ በሎቶ ከ1-5 በተገለፁት መሰረት የተዘረዘሩትን ግዥዎች የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

መ/ቤቱ ናሙና ያስፈልጋቸዋል ለሚላቸው እቃዎች በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡

በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 817 00 40 ወይም በ09 18 25 26 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here