የደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2017 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 ቋሚ እቃ፣ ሎት 2 የኤሌክትሪክና የቧንቧ እቃዎች፣ ሎት 3 አትክልት፡ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ቃሪያ ወዘተ፣ ሎት 4 የተዘጋጀ ሽሮ፣ በርበሬ እና አተር ክክ፣ ሎት 5 ሩዝ እና ሎት 6 የእርድ ስጋ፣ ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
ግዥ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 033 111 46 84 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት