በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2017 በጀት አመት ለሚገነባው የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የሚውሉ ሎት 1 75ሜ3 GRP የውሃ ታንከር አቅርቦትና ገጠማ እና ሎት 2 ጀነሬተር stand by power 315 KVA አቅርቦትና ገጠማ በዘርፉ በተሰማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ዋና /ኦርጅናል/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም የተከለከለ በመሆኑ ተቀባይነትም የለውም::
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ወልዲያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ:: የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን 11፡00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም::
በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታው ማቅረብ ይችላሉ::
ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል::
ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው::
ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ