በጨረቃ ላይ የተለዩት ቀጣናዎች (ቦታዎች)

0
127

የጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ለሳይንሳዊ ግኝት እምቅ አቅም ይኖራቸዋል ተብሎ የታመነባቸው ዘጠኝ የማረፊያ ክፍሎች ተለይተው ይፋ መደረጋቸውን ስፔስ ቮዬጂንግ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል::
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (NASA) ‘’Artemislll’’ በተሰኘው ተልእኮ በ2026 እ.አ.አ ወደ ጨረቃ ለሚያመጥቃቸው መንኮራኩሮች ከዚህ ቀደም ባልተዳሰሰው የጨረቃ ደቡብ ወልታ ዘጠኝ ማረፊያ ቦታዎች ወይም ክልሎች መለየቱን አስታውቋል::
የተለዩት ዘጠኙ ቀጣናዎች በስነ ምድር ባህሪያት (Geological characteristics) ልዩነት ያላቸው እንዲሁም ለሳይንሳዊ ግኝቶች እምቅ ዓቅም ይኖራቸዋል ተብለው የታመነባቸው መሆናቸውን ድረ ገፆች አስነብበዋል::
የጠፈር ምርምር ተቋሙ በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ ትኩረት አድርጐ ቀጣይነት ያለው ዳሰሳና ጥናት በማካሄድ ወደ ፊት ወደ ማርስ ለሚካሄዱ ተልእኮዎች ማረጋገጫ ሆኖ እንደሚያገለግል ነው የተጠቆመው::
የጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ ቀጣና ትኩረት ያልተሰጠው ጥላ ያለው ወይም ጨለም ያለ፣ ወጣ ገባ ወይም ዳገት ቁልቁለት የሚበዛው፣ ከተፈጥሯዊ ሀብት ውኅ፣ በረዶ የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሎ ስለሚታሰብ ለቀጣይ የጠፈር ዳሰሳ ዒላማ መሆኑ ነው የተብራራው::
በናሳ የጨረቃ ሳይንሳዊ ምርምር መሪ የሆኑት ሳራ ኖቤል በ “Artemislll” ተልእኮ የጨረቃ ደቡብ ዋልታ ማረፊያ ክልል ቀደም ብሎ በአፖሎ ተልእኮዎች ማረፊያ ከነበሩት ቦታዎች የተለዩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል:: ለአብነት ማረፊያ ቀጣናዎቹ ቀዝቃዛ በጥላ የተሸፈኑ አካባቢዎች መሆናቸውን እና፣ የተለየ ሳይንሳዊ ግንዛቤ እንደሚያስጨብጡ እምነታቸው መሆኑን አስምረውበታል::
ከጨረቃ ወደ ማርስ የመምጠቅ ኘሮግራም ፅህፈት ቤት ረዳት ምክትል አስተዳዳሪ ላኪሻ ሃውኪንስ ቀጣዩ ተልእኮ ወደ ጨረቃ በመመለስ ባልተዳሰሱ ቀጣናዎች ላይ ምርምሩን አድርጐ ወደ ሌላኛው ምእራፍ ለመሸጋገር መሆኑን ነው በአፅንኦት የገለጹት::
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም ዋና ተመራማሪው ጃኮብ ብሌቸር “Artimislll” ተልእኮ የጠፈር ተመራማሪዎች በጨረቃ ደቡብ ዋልታ አካባቢ ሲያርፉ የመጀመሪያ ጊዜያቸው መሆኑን ጠቁመው ከአፖሎ ተልእኮ በተለየ በላይኛው ገፅታ አቀማመጡ፣ በብርሃን መጠን፣ ግንኙነት ለመፍጠር ምቹነቱ ወዘተ መምረጫ መስፈርት ሆነው ማገልገልቸውን ነው ያሰመሩበት::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here