በደቡብ ጎንደር ዞን የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ዘዴ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ መሆን አለባቸው፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ስለሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ኮሌጁ ከ20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ግዥ ሲፈጽም መንግስት በሰጠው ውክልና መሰረት ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
- ኮሌጁ ከ10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ግዥ ሲፈጽም ሁለት በመቶ የዊዝሆልዲንግ ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡
- በሰነዱ ላይ የተጠቀሰዉ ቁጥር ብዛት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒዉን ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ተገልጾላቸው ያሸነፉትን የዕቃ ጠቃላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪ ዋስትና /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናዉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በ4፡10 ይከፈታል፡፡
- ዉድድሩን በተናጠል የማናማወዳድር መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን ተወዳዳሪዎች ሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊዎች እቃዎቹን ኮሌጅ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 141 00 31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አድራሻ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ (በጌምድር መ/ራን ትም/ኮሌጅ)
የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ