በአብክመ ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 የቤትና የቢሮ እቃዎች እና ሎት 6 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ የመወዳደሪያ መስፈርቱ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ግዥው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በእ/የመ/ደ/ሆ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እ/መ/ደ/ሆ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ የሚገዛቸውን እቃዎች ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የቀረቡትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው አንድም እቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች አይነት ስፔስፊኬሽን/ መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ሆስፒታሉ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል፡፡
- ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡oo ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስትሞሉ ሥርዝ ድልዝ (በፍሉድ) የጠፋ መኖር የለበትም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በስሙ የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት፡፡
- ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ30 ቀን ይሆናል፡፡
- በተለያየ ምክንያት የጨረታ ሰነዱ ችግር ቢኖርበት ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስተካከያ የሚደረግበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ለማሸነፍ ሲባል የተወሰኑትን እቃዎች በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አላቀርብም /ገቢያ/ ላይ የለም ማለት አይቻልም፡፡
- በዚህ ሰነድ ላይ ያልተገለፀ ሀሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 058 440 09 13 ደውለው መጠየቅ ችላሉ፡፡
የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል