ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
124

በአዊ ሔረሰብ አስተዳር መምሪያ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ከውስጥ ገቢ በጀት  በግልፅ  ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 ህትመት፣ ሎት 2 መድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ስለዚህ የሚከተሉትን  መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የመድኃኒትና ህትመት አይነቶችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ ቢሮ ቁ 35 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ደረሰኝ በመ/ሂ1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ፖስታ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በእን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ/ ወይም ቢሮ ቁጥር 35 ጨረታው በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ቡ ቢሮ ቁጥር 35 ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. በሎት 1 ላይ የሚወዳደር አንድ ተጫራች በዚሁ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የህትመት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡ በዚሁ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በማሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን ህትመቶችንና የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎችን እን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ እን/ከተ/አስ/እን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ/ ቢ.ቁ 35 24 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቀጥር 058 227 01 65 /09 18 13 99 85 /09 18 67 04 42/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. የእን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ እንደ በጀት አቅሙ ሃያ በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በሎት 2. ወይም በመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ የሚወዳደር ተጫራቾች አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ ዋጋ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ:- የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት  በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here