ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.ሎት 1.የበቀሎ ሰብል ሽያጭ፣ ሎት 2.ያገለገሉ እቃዎች /ባዶ ጆንያ/ ሽያጭ፣ ሎት 3. የትክተር ጎማ ካላማዳሪ ግዥ እና ሎት 4. የፎሚጌሽን ሽራ ግዥ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአሽናፊው የሚሸጡትን መሸጥ እና የሚገዙትን መግዛት ይፈለጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው ፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ዋጋው ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው ወይም አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛውን እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አይደለም፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ00 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 8፡00  ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ የዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡
  9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10በመቶ /አስር በመቶ/ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፍቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ መርጦ መሙላት አይቻልም፡፡
  12. አሸናፊው የአሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ይወስዳል ያቀርባል፡፡ማንኛውም ወጭ አሸናፊው የሸፍናል፡የሚሸጡት ሆነ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡አሽናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡
  13. አሸናፊው የአሸነፈበትን ሽያጮችና ግዥዎች በፍትህ ውሉ ከተመረመረ ወይም የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል፡፡
  14. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  15. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 18 27 81 46 /09 18 27 8396 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here