ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

የጨረታ ሰነድ ቁጥር KFW 02/2

በጀርመን መንግስት የልማት ትብብር ባንክ /KfW/ የደቡብ ወሎ ደን ልማት እና ብዝሀ ህይወት ሀብት ጥበቃ ፕሮጀክት ጅፒኤስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ60.00 /ስልሳ ብር/ በመግዛት ከድርጅቱ በመውሰድ መጫረት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የባንክ ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/ በማስያዝ በፖስታ በማሸግ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ  ግዥ ቢሮ  ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ ሳጥኑ በጨረታ መዝጊያው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3:30 በድርጅቱ ግዥ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  7. ከ20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ለሆኑ ግዥዎች ቫቱን በግማሽ በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን አናሳውቃለን፡፡
  8. መ/ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 62 06 ወይም 09 18 18 73 68 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአብክመ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን

ባ/ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here