የእብናት ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ለአብናት ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር በጨረታ የድርጅት 01 G+2 የቅይጥ 01 G+0 የመኖሪያ 03 G+0 የመሬት ሊዝ በግልፅ ጨረታ አዉጥቶ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በእብ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋዉን በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት የተሰራዉን (ሲፒኦ) እና ሰነድ የተገዛበትን የ300.00 /የሶስት መቶ ብር/ ደረሰኝ ሁለቱን በአንድ ላይ በማድረግ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ ገቢ አድርጎ ኦርጅናል ሰነዱን የእ/ከ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋይናን ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ 4፡40 ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ ለካሬ ለድርጅት 00 /አምስት በመቶ ብር/ ለሌሎቹ ቦታዎች ግን 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ለድርጅት አስራ አምስት በመቶ ለመኖሪያ ሃያ በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ የድርጅት G+2 ሌሎቹ ደግሞ G+0 ነዉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የቦታው አገልግሎት ለእያንዳንዱ ምድብ ከሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠ ይሆናል፡፡
- በአጭር ጌዜ ውስጥ ወደ ግንባታ የሚገባና የሚያጠናቅቅ መሆን አለበት፡፡
- ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ድርጅት 01 መኖሪያ 03 ቅይጥ 01 ነዉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ጽ/ቤት በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእብናት ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት