ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት ለጭ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ማለትም ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ የቆዳ ጫማ ውጤቶች  ፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ የተዘጋጀ ፣ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማና ባትሪ እና ሎት 8 የአዳራሽ የመሰብሰቢያ ወንበር ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉ በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ቢሮ ቁጥር 7 ከረዳት ገ/ያዥ ድረስ በመምጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦዉ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸዉንና አድራሻቸዉን በመፃፍ በጭልጋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚዉል ሲሆን ፖስታዉን እስከተገለፀዉ ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛዉ ቀን ጠዋት በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ዉስጥ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  11. አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይቻላል፡፡
  13. አሸናፊዎች የሁሉም ምድብ ዕቃዎች የሚያቀርቡት በጭ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ለዉድድር ከቀረቡ በኋላ ሀሳባቸዉን መለወጥ /ማሻሻል/ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ ከግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 11 57 ወይም 09 18 43 38 46 በመደወል መረጃ  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. ጨረታዉ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለዉ ጨረታዉ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
  18. የጨረታውን አሸናፊ የምንለየዉ በጥቅል ድምር ወይም በተናጠል ይሆናል፡፡
  19. ናሙና የሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች በናሙናው መሰረት የሚቀርብ መሆኑንና የእቃ ናሙናው በጭ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት  በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 የሚገኝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሁሉንም አይተሞች መሞላት አለባቸዉ ክፍት መሆን የለበትም፡፡

በየገፁ የድርጅትዎ ማህተምና ፊርማ ይደረግበት፡፡

የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here