በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ2017 በጀት ዓመት የሰርቨር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ የሆነ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጀቱ ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፣ ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡ በቀረቡት እቃዎች ላይ ችግር ቢፈጠር የመመለስ /የመቀየር/ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፋበት የእቃ ዋጋ ድምሩ ከ10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሁለት በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- የአሸነፉበት የእቃ ድምር ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች እስከ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዘው መቅረብ አይፈቀድም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከአሸነፊ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
- የሚገዙት እቃዎችን ዝርዝር ከመ/ቤቱ ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/2004 ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት በ16 ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይሆናል፡፡
- ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ አገልግሎቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም Email gechmog@gimail.com ፋክስ 033 331 15 72 እንዲሁም በስልክ ቁጥር 033 431 07 99 /033 431 12 23 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የወልድያ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት