የወልድያ ከተማ ውሃ አገ/ት (ድርጅት) የሁለት ዓመት ማለትም ከ2015 እስከ 2016 በጀት ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች በጋዜጣ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱን (ድርጅቱን) ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰ፡፡
- በሂሣብ ምርመራው /ኦዲት/ ተግባር ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት CV /የትምህርት ደረጃ/፣ የሥራ ልምድ ወዘተ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተያዘ /የተገባ/ የቅጥር ውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የበጀት ዓመት(ቶች) ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ሁለት በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያከናውኑትን ተግባር በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጀቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ)፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት /ቲን/ እና ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) ወልድያ ከተማ ውሃ አገ/ት መ/ቤት (ድርጅት) ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዓመት ኦዲት ሥራ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትን የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር /ማስኬጃ ውል/ በማዘጋጀት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ 3፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ Email gechmog@gmail.com ፋክስ 033 331 15 72 በስልክ ቁጥር 033 431 07 99 /033 431 12 23 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት