(ቁጥር 01/17)
የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ልጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሚሰሩ ተፋሰስ ሥራዎችን ሎት 1 ከሞላ ይመር ቤት እስከ ሙሀመድ አስፋዉ ቤት፣ ሎት 2 ከሙሀመድ አስፋዉ እስከ ያሲን ቤት፣ ሎት 3 ከያሲን ቤት እስከ ከድጃ ቤት ድረስ አዲስ ተፋሰስ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ደረጃ 9(ዘጠኝ) እና በላይ የሙያ ፈቃድ ያላቸው (ደረጃ 10 አያካትትም)
- የሚጫረቱበት ጨረታ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት በመቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 79,000.00፣ ሎት 2 90,000.00 ሎት 3 97,000.00 በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋጋ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሥራዉን ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳብን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመርሳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/04/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በ31ኛው ቀን በ10/04/2016 ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም 09 13 28 23 42 /09 35 21 25 15 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፋቱን ሎት የማቴሪያልና የጉልበት ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ነዉ፡፡
- ሥርዝ፣ ድልዝ እና ፍሉድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ከጨረታ ዉጭ ያደርጋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ጸንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀን የጸና ይሆናል፡፡
- ሶስት እና ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ አርቴሚቴክ ዉጤት ልዩነት ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ በላይ ከመጣ ተቀባይነት የለዉም ከ3 በታች ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ ከ አንድ በመቶ በላይ የአርቲሜቲክ ልዩነት ተቀባይነት የለዉም፡፡
የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት