የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለወረዳ ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ እና ልዩልዩ የቋሚ አላቂ እቃዎች 20,000.00 (የጨረታ ማስከበሪያ)፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች 3,000.00 (የጨረታ ማስከበሪያ) እና ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000.00 /የጨረታ ማስከበሪያ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችኃል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ቲን ሰርትፊኬትና ቫት ሰርፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ (በግልጽ ጨረታ) ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በሥራ ስዓት የጨረታ ሰነዱን አን/ጓ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ሥርዓቱ የጽህፈት መሳሪያ እና ልዩልዩ የቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ እና የህንፃ መሳሪያ በሎት አሸናፊ የሚመረጥ ሲሆና ሌሎች ግን በአይተም ይሆናል፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር በሎቱ በተቀመጠው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በወረዳው የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1 /ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አዊ ብሔ/አስ/ዞን አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ ለ16 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አንከሻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 08 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣ ነገር ግን 16ኛው ቀን (የሚከፈትበት ቀን) ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 05 20 /058 224 00 03 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአንከሻ/ጓ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት