ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

የወልድያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ መገልገያ ቁሳቁሶችን፡፡ ሎት 1. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2. አነስተኛ የእጅ መሳሪያዎች፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የህትመት ስራዎች እና ሎት 5. ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፋ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የሚገዙ አቃዎችን በአይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ፣ለህትመት ቋሚ እቃዎች 10.00/አስር ብር/ ፣ለጽዳት እቃዎች 5.00 /አምስት ብር/ ፣ለህትመት ስራ 20.00 /ሃያ ብር/ ፣ አነስተኛ የእጅ መሳሪያዎች 5.00 /አምስት ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10.00 /አስር ብር/ በመክፈል ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡ ለሞሉት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ አንድ በመቶ የከፈሉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሸግ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  6. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ በወ/ወ/ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል ፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ህዳር 17/2017ዓም ከረፋዱ 3፡30 ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው በሎት የሚወዳደር ሲሆን፤ በሎት ምድብ የምትወዳደሩ የተፈለገውን እቃ አጠቃሎ የማይሞላ እና ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡የጨረታው አሸናፊ የመጓጓዣና የመጫኛ መገጣጠሚያ ወጭዎችን ይሸፍናል፡፡
  9. አሸናፊዎች ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሰነድ የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወ/ወ/ፍ/ቤት ለገንዘብ ያዥ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የአብክመ ገ/ኢ/ል/ቢሮ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ዓ.ም ያወጣውን የጨረታ ህግ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 83 08 በመደወል መረጃ ማግኘት የቻላል፡፡

የወልድያ ወረዳ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here