ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

የሰሜን ወሎ ዞን የጉባ ላፍቶ ወረዳ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቶች ያሸነፍትን ሎት በተሰጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ እና  ማጓጓዝ ፣የማስጫን እና የማውረጃ እንዲሁም ወጭውን በራሳቸው በመሸፈን ጉ/ላ/ወ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ወደ ሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቶች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት በ5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፋትን እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቶች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የኖርባቸዋል፡፡
  7. ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 8 የተጠቀሱትን  በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን  በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል  መውሰድ ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ከነ ማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ የጨረታ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 3፡00 ላይ ታሽጎ 4፡00 በግዥ ንብረት አ/ስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል ፡፡ ለሁሉም  የጨረታ ማስታወቂያ መክፈቻ ቀኑ  በአል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ ለሁሉም ጨረታዎች በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ ማሳወቅ አለባችው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00/ሰላሳ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ዋናውን ጨረታ  በፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊው ውል ከወሰደ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይለቀቃል፡፡አሸናፊው የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተገጋገጠ የባንክ ዋስትና ዋናውን የዋጋ ጠቅላላ ዋጋ በማስያዝ በጉ/ወ/ፍ/ጽ/ቤት  በኩል ውለ ይወስዳል፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፍትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም  እቃው በሙሉ በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀረብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል ፤በህግም ያስቀጣል፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ስለትክክለኛነቱ የጥራት ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡

ውድድሩ በሎት በመሆኑ ማንኛውም ተጫራቾች ሁሉንም የእቃ አይነቶች የመጫረቻ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ አንድም ሆነ ከአንድ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

የጉባ ላፍቶ ወረ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here