የደ/ጐን/አስ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. ህትመት፣ ሎት 3. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች እና ሎት 5. ሌሎች ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሎት ከጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ 1% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በ50.00 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨሬታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨሬታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠዉ ወይንም የሚለዩት በሎት ወይንም በጥቅል ዋጋ ነዉ፡፡
- አሽናፊ ድርጅት የአሸናፈዉን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራጨቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፍቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይንም በህጋዊ ወኪላችዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0584410386 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ጐን/አስ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት