ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
88

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ንበረት ለሆኑት የተለያዩ ከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማ ከነ ካላማዳሪዉና ከነፍላፑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው::
3. በስሙ የታተመ ማህተምና ደረሰኝ ያለዉ::
4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
6. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
7. ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 200,000,00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 16/03/2017 ዓ.ም 01/04/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1,500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ::
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በእለቱ በ01/04/2017 ዓ.ም በ4፡30 ይከፈታል:: ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት እንገደዳለን::
11. አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል::
12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here