የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 5. የብስክሌት ጎማ፣ ሎት 6. የደንብ ልብስ እና ሎት 7. የመኪና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ በ100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታው ሰነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
4. የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ የተገለጸ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሰነዱ ጋር አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
6. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 013 በመቅረብ ወይም በስ.ቁ 058 226 27 19 ወይም 058 220 52 69 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት