የጨረታ ቁጥር 001/ ፊ/የሀ/ግዥ/2017
በምዕ/ጐጃም ዞን ለፊቤላ ኢንዱስትሪያ ኃ/ የተወሰነ የግል ማህበር በቡሬ ከተማ ለፋብሪካዎች ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ ሎት. 01 የፅህፈት እቃዎች እና ሎት 02. የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱና በናሙና የቀረቡትን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከስዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የሥራ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት /ከሰኞ እስከ ቅዳሜ/ ጠዋት ከ 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከስዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት እና በ16 ተኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተወደዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር
09 10 69 31 95 /09 10 15 63 45 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፊቤላ ኢንዱስትሪያ ኃ/ የተወሰነ የግል ማህበር