በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሚገዙ ግዥዎች ማለትም ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት 2. የውሃ መገጣጠሚያ ፣ሎት 3. ኤሌክትሮመካኒካል ዕቃዎች እና ሎት 4 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች ያለዉን መስፈርት አሟልተዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፤ የእቃው ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ድረስ በዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በፖስታዎች በማሸግ መስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅት ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን የመክፈቻ ቀኑ ማለትም በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ለተወዳደሩበት በየሎቱ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1. ብር 4,000.00 ፣ ለሎት 2. ብር 10,000.00 ፣ ለሎት 3. ብር 10,000.00፣ ለሎት 4. ብር 2,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ነው፣ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሚገዙ እቃዎች አገልግሎቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅፆችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 /09 74 50 58 99 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡
የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት