የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃወች፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ ሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
2. ሎት 1. የጽ/መሳሪያ ፣ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ስፔር ፓርት)፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ ሎት ልብስ ሎት አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ሌተር ኦፍ ክረዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመሂ 1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ዋጋ አንድ በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ በማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅጽ ሞልተው ማቅብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ይከፈታ፡፡
5. የተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዜ ዓመታዊ ውል ስለሚሆን የጨረታውን ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
7. አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በጥቅል ሰለሆነ የሙሉ ዕቃ ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ከወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና ዕቃዎችን መተማ ወረዳ ንብረት ክፍል በዝርዝር ማሰረከብ የሚችሉ፡፡
9. ሰለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 02 68 እና 058 331 00 47 በመደወል ማግኝት ይችላሉ፡፡
10. አሸናፊው ዕቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሥርዝ ድልዝ በማድረግ ሌላ ተመሳሳይ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11. የጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሰባሰቢያ ሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፀለን፡፡
12. አሸናፊው ድርጅት የውል ማሰከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም ሲፒኦ በማስያዝ በወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መውሰድ የሚችል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት