ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደባይ ጥላት ግን ወረዳ በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ቤት በ2017 የበጀት አመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልገው ማቴሪያል ወይም ጠጠር የሚመረትበትን ቦታ ማዘጋጃ ቤቱ የሚያሳይ ሲሆን በጥራት የሚሰራ ሆኖ ከተጫራቾች መካከል አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ የማሽን ፈቃድ ያላቸው አካላት ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በወጣው የሥራ ዝርዝር መሰረት ሁሉንም ወጭ የሚችል ማለትም ለመንገድ የሚያስፈልገውን ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውረጃ (ሎቬድ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይቻላል፡፡
5. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ግዥዉን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከዜሮ ነጥብ አምስት ያላነሰ እና ከሁለት በመቶ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን ተወስኖ በጨረታ ጥሪዉ እና ሰነድ ዉስጥ መገለፅ አለበት፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ የሆኑ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቁይ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የግዥ ጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸዉን፣ ፊርማቸዉን፣ ሙሉ አድራሻቸዉን እና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ፓስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
9. ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. የማሽን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
11. የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆየው ለ21 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባልተገኙበት ቢሮ ቁጥር 07 ጋዜጣው በወጣ በ22ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ተጫራቾች ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
14. በዉድድሩ የተገኘዉ ዋጋ ሳይቀየር መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
16. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ወይም ሎት ሞልቶ ካቀረበ ይሆናል፡፡
17. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገድ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል ወይም ቁሳቀስ ትራንስፖርት ቦታው ድረስ እራሱ የሚያጎጉዝ ይሆናል፡፡
18. አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
19. ተጫራቾች የጨረታውን መጠን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
20. ሥርዝ ድልዝ ካለው ልዩ ፊሪማ መቀመጥ አለበት ፤ ልዩ ፊርማ ከሌለው ተቀባይነት የለውም፡፡
21. አድራሻችን በምስራቅ ጎጃም ዞን/ደ/ጥ/ግ/ወ/ቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአዲስ አበባ 284 ኪ/ሜትር ከባህርዳር ከተማ 324 ኪ/ሜትር፣ በደብረማርቆስ ቁይ 60 ኪ/ሜትር ላይ ትገኛለች፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 0931842543/0920506944 መደወል ይቻላል፡፡
22. ማሳሰቢያ፡-ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ(ሎቬድ) አሸናፊው የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here