የጨረታ መለያ ቁጥር 03/2015
የእንጅባራ /ከ/አስ/ከተማ/መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለጽ/ቤት በፓኬጅ ቁጥር AMH /INJEBARA/CIP/GS01/23/24 ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ. ሎት 2. AMH/INJEBARA/CIP/GS 03/23/24 እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል::
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው::
3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዘው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ከህዳር 16/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ 21 ቀን ይሆናል::
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት እንጅባራ ከተማ አስ/ከተማ/መ/ልማት/ጽ/ቤት ግዥ/ፋን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ::
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እንጅባራ ከተማ አስ/ከ/መ/ ል/ ጽ/ቤት ግዥ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም 3፡00 ማስገባት ይችላሉ::
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንጅባራ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን በቀን 07/04/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል:: የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል::
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአላቂ የጽህፈት መሳሪዎች ለሎት 1. ብር 5,627.00 /አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ሰባት ብር/ ኤሌክትሮኒክስ ለሎት 2. ብር 4,800.00 /አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
10. የጨረታው አሸናፊ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ውል በሚይዝበት ወቅት ማስያዝ አለበት::
11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች እስከ እንጅባራ ከተ/ አስ/ከተ/መ/ል/ጽ/ ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ ወይም ማስረከብ ይኖርበታል::
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ጨረታው ሲሞላ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት አለበት::
13. ለተጨማሪ መረጃ የእን/ከ/አስ/ከተ/ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ግዥፋ ን/አስ/ ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 00 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
14. የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ይሆናል::
እንጅባራ /ከ/አስ/ከተ/መሰረተ ልማት ጽ/ቤት