ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
100

በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ የፅፅቃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት ለኮሌጁ አገለግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 1. የኮንስትራክሽን እቃዎች ሎት 2. የደንብ ልብስ ሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
3. የግዥው መጠን 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለምትወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናል እና ቅጂ በማለት በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በፅ/ቴ/ሙ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በግልጽ ይከፈታል፡፡
10. ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ነው ከሎት ውስጥ አንዱን እቃ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ 50.00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
12. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን ሙሉ አድራሻችን እና ማህተማቸውን በማረጋገጥ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ ውሉን ክወስደበት ቀን ጀምሮ እቃዎችን በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
14. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በፅ/ቴ/ሙ/ ኮሌጅ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 21 03 21 77 /09 53 27 14 74 /09 14 32 51 34 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፅፅቃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here