ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
131

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዝብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ /አስ/ ቡድን በ2017 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የአዳራሽ ግንባታ፣ ሎት 2. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 3. ሲሚንቶ እና ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
5. የግዥዉ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. የእቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ለግንባታ ሲሆን 50.00 /ሃምሳ ብር/ ለእቃ ግዥ በመክፈል ጎ/ቆ/ወ/ፋይናስ ቡድን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ግዥ አንድ በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ለእቃዎች እና ለህንፃ ግንባታ ደግሞ 100,000.00 አንድ መቶ ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላዉን ዋጋ አስር በመቶ ለእቃ ግዥ ሲሆን ሃያ አምስት በመቶ ደግሞ ለግንባታ ሥራ /በሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለህንፃ ግንባታው ተጫራቾች የሚካትተው ከ ደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 ብቻ ይሆናል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የአዳራሽ ግንባታውን የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎ/ቆ/ወ/ገንዘብ//ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 16/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በቀን ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
10. ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎ/ቆ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ታህሳስ 6/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች ለእቃዎች ግዥ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎ/ቆ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 16/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይሮርባቸዋል፡፡
12. ጨረታው በቀን 1/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
13. ጨረታውን ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎ/ቆ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን 01/4/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎ/ቆ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
16. በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለ መስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
17. መ/ቤቱ እቃዎችን ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
18. አሸናፊው የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
19. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
20. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ የማቅረብ መብት አላቸው፡፡
21. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል ሲይዝ የአገልግሎት ክፍያ በራሱ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
22. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here