ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
120

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳር የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመቱ ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የ1ኛ የጽህፈት መሳሪያ፣ 2ኛ. ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ 3ኛ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ 4ኛ ብትን ጨርቅ፣ 5ኛ የስፖርት ትጥቅ እና እቃዎች እንዲሁም 6ኛ. የተዘጋጁ ጫማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የሚገዛው የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችኋል ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በየሎቱ በጥቅል ድምር ነው፡፡
6. የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ለጽህፈት መሳሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ለተዘጋጁ የደንብ ልብሶች 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ለብትን ጨርቅ 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ ፣ለስፖርት ትጥቅ እና እቃዎች 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለተዘጋጁ ጫማዎች 5,000. /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ለስድስት ወር የሚቆይ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በወረዳው የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው ከተገለጸው ውጭ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ዚገም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚገም/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን (የሚከፈትበት ቀን) ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
10. ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ውጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
11. ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ ዚገም ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
12. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
13. መ/ቤቱ ሃያ በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. የደንብ ልብስ ተጫራቾች የሚሞሉትን ደንብ ልብስ ሳምፕል ናሙና/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ደንብ ልብስም በናሙና መሠረትና በደንብ ልብስ አጠቃቀም መመሪያ ሁኖ ናሙናው ተቀባይነት ያለገኘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 556 87 60 /09 13 71 74 22 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here