የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ 56 እና ለድርጅት 3 አገልግሎት በድምሩ 59 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
1. ጨረታው በአየር ላይ ከ23/03/2017 እስከ 04/04/2017 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡ ስለዚህ መጫረት የሚፈልጉ ሰው/ድርጅት የጨረታ ሰነዱ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከ23/03/2017 እስከ 04/04/2017 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ይሆናል፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋው 04/04/2017 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
4. ጨረታው የሚከፈተው 05/04/2017 ዓ/ም በ 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
5. ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው፡፡
የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፣
በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ለድርጅት አስራ አምስት በመቶ እና ለመኖሪያ ሃያ በመቶ የተከፈለበት፡፡
ኦርጅናል /ዋናውን/ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
6. የጨረታ ቦታዎችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው ኘላን መመልከት በአካል መጎብኘት ይቻላል፡፡
7. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ