ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

0
98

በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የቡሬ ከተ/አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቡሬ ከተ/አስ/ሴክተር መ/ቤቶች እና ለCIP ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈት መሳያዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 4 የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 7 የጫማ ግዥ፣ ሎት 8 የተዘጋጁ ልብሶች እና ሎት 9 ብትን ጨርቅ ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን በእያንዳንዱ ሎት 1 ብር 11,500.00 (አስራ አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር)፤ ሎት 2 ብር 12,000.00 (አስራ ሁለት ሽህ ብር)፣ ሎት 3 ብር 2,500.00 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ሎት 4 ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ ብር)፣ ሎት 5 ብር 2,500.00 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር) እና ሎት 6 ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ ብር) ሎት 7 ብር 3,000.00 (ሶስት ሽህ ብር ሎት 8 ብር 4,500.00(አራት ሽህ አምስት መቶ ብር) እና ሎት 9 ብር 1,900.00 (አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ4፡00 ታሽጎ በ4፡15 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡
አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ሲሆን በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ እና እቃዎችን በቡሬ ከተ/አስተዳደር ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
ሁሉም እቃዎች በዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ የሚፈጸም መሆኑ አቅራቢው ሙሉ እምነት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 11 00 /111 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here