ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

0
96

የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በድምር/ሎት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ጽዳት እቃዎች ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 5 የመኪና እቃ ሎት 6 የደንብ ልብስ በየሥራ ዘርፋቸው ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊዎቹ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተወዳዳሪዎች
በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ማንኛውንም የሚጠየቁትን መረጃ ማሟላት የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው 200‚000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆነቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ አይነት 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በ16 ተኛው ቀን ኦርጅናሉን በማስገባት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት 5፡00 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረብ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
.ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ውል መፈጸም ኖርባቸዋል፡፡ ሥራው ከተጠናቀቀ እና ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀን ጸንቶ ይቆያል፡፡
መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 20 47 88 84 ይደውሉ፡፡

የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here