በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ /ፖ/ቴ/ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 .ጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት 2 ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት 4 ጨርቃ ጨርቅ ፣ ሎት 5 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በኮሌጁ ደረሰኝ ጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ጠቅላላ የዋጋውን ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀናት በአ/ዘ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ ከህዳር 23/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን በሁሉም ሰነዶች የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ ፊርማ እና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላት እና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
በ15ኛ ቀን የበዓል ቀን እና የህዝብ የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ማለትም በ16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል፡፡
ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝር እና ስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊው ድርጅት /አካል/ ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፉት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
አሸናፊው በውሉ መሰረት ካላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ ይሆናል፡፡
አሸናፊው የሚለየው እንደአስፈላጊነቱ በተናጠል ወይም በሎት (በጥቅል) ዋጋ ይሆናል፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሆነው ተወዳዳሪ ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት አ/ዘ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋን አስር በመቶ /አስር በመቶ/ በማስያዝ ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 444 08 44 /162 በመደወል ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘጋጀው ስፔስፊኬሽን ውጭ የራሱን ስፔስፊኬሽን ማስቀመጥ አይችልም፡፡
አዲስ ዘመን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ