ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ውጤቶች፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 6 የመኪና ጎማና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፡፡
የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነድና የእቃ ሳምፕል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 003 ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች 8,000.00 ፣ ሎት 2 የፕሪንተር ቀለም 3,500.00 ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ 3,200.00 ፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ውጤቶች 2,000 ፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች 8,000.00 እና ሎት 6 የመኪና ጎማና መለዋወጫ እቃዎች 26,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ስፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች በማድረግ በአብክመ መንገድ ቢሮ በግዥ /ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ የቴክኒካል ፖስታው ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ዶክመንቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ይታሸግና ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻዉ ዕለት የህዝብ በዓል እና ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 18 84 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 63 50 /058 320 86 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አብክመ መንገድ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here