ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 የበጀት አመቱን ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች ሎት 1 የምግብ አቅረቦት፣ ሎት 2 የልብስ እጥበት እና ሎት 3 የጥበቃ አገልግሎት ማቅረብ እና መጠበቅ የሚችሉ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላውና የከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚቀርቡ የምግብ እና የሚታጠቡ የልብስ እጥበት አይነት እና የጥበቃ አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናን ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሪ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ከ23/03/2017 እስከ 07/04/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ08/04/2017 ጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
አሸናፊው የሚለየው በሎት ዋጋ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 00 54 /058 331 01 75 ማግኘት ይችላሉ፡፡
አሸናፊው አገልግሎቱን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሥርዝ ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ መምርያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
መ/ቤቱ ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ ይችላል፡፡
በመ/ቤቱ ለምግብ እና ለእጥበት አሸናፊው የሚሰጠው መብራት፣ ውሀ እና ቤት ኪራይን በነፃ ሲሆን ከግቢ ውስጥ የመብራት እና የውሀ መጥፋት ቢገጥም በራሳቸው የሚያቀርቡ መሆኑን እየገለፅን ይሄን ታሳቢ በማድረግ ዋጋውን እንድትሞሉ ያሳውቃል፡፡
አሸናፊው ድርጅት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለው የምግብ ቤት እና የላውንደሪ ቤት ገብቶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
አሸናፊው በመሥሪያ ቤቱ ባለው የስነምግብ ባለሙያ በሚያቀርበው የሰው ሀይል ብዛት ብቻ ምግብ ማቅረብ የሚችል፡፡
የልብስ እጥበት በሚሰጠው የቆሸሹ ልብሶች ብዛት ይሆናል፡፡
ጥበቃ በግቢው ውስጥ ከተመደበበት ቦታ ለ24 ሰዓት መጠበቅ የሚችል፤ የጦር መሳርያ ልምድ ያለው፤ የተጠየቀውን መስፈርት ማሟላት የሚችል እና ተደራጅቶ መቅረብ የሚችል መሆኑን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here