ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
95

ደቡብ ጐንደር አስ/ዞን የደብረ ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ መገልገያ እቃዎች ለተለያዩ ትም/ክፍሎች ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎችና ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፣ ሎት2. ኤሌክትሪክ፣ ሎት3. ኤሌክትሪክስ /ኮምፒውተር እና የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎች፣ሎት4. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 5. የቴክስታይል እቃዎች፣ ሎት 6. የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣ ሎት7. የጽዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግዥው መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያስዙ ከሆነ በኮሌጁ የውስጥ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመቁረጥ ደረሰኙን ኮፒ አድርገው በጨረታ ፖስታው ውስጥ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በደ/ታ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውልና በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የሚከፈትና አሸናፊው የሚለይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡
ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በቫት ከሆነ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰውን መለያ /ስፔስፊኬሽን/ መቀየር ወይም ስያሜ መስጠት ወይም የማስተካከል ስራ ከተሰራ እና ሥርዝ ድልዝ ካደረጉት ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች ከግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ በተጠየቀው ስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው፡፡ የደረሰኙ ቁጥሩ ተከታታይ ካልሆነ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ይሆናል፡፡
አሸናፊው ድርጅት በአሸነፈበት ዕቃ የዋጋ ድምር ውል በመውሰድ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቶች ላወጡት ዋጋ ኮሌጁ ተጠያቂ አይሆንም ፡፡
ስለጨረታው ማብራሪያ መጠየቅ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመገኘት ወይም በስ-ቁጥር 058 441 04 47 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ደብረ ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here