ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ፣

0
130

በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ በኮን ከተማ የሚገኘዉ የኮን ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የጋርመንት /የልብስ ስፌት እቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 5 የጂኤም ኤፍ ኤ እቃዎች፣ ሎት 6 የኮንስራክሽን እቃዎች፣ ሎት 7 የአይሲቲ የት/ርት እቃዎች እና ሎት 8 ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የሚገዙ የእቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከየካቲት 23/03/2017 ዓ.ም እስከ 7/04/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ /መግዛት/ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የእያንዳንዱ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
የጨረታዉ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ማሻሻያ ማረግና እራሳቸዉን ከጨረታዉ ማግለል አይቻልም፡፡
ዉድድሩ የሚካሄደዉ በሎት ድምር ዉጤት ነዉ፡፡
ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ መጠን አንድ በመቶ የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና በጥሪ ገንዘብ ማሰያዝ አለባቸዉ፡፡
ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ዉጭ መሆኑን መግለጽ አለባቸዉ፡፡
ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋለው፡፡
አሸናፊዉ በተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት ንብረቱን እቃዉን ማቅረብ አለበት፡፡ ከተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን ዉጭ ይዞ ቢቀርብ በሚደረሰዉ ኪሳራ ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም ንብረቱ በባለሙያ ተፈትሾ ነዉ ገቢ የሚሆነዉ፡፡ ጥራት የጎደለዉ እቃ ኮሌጁ ያለመረከብ መብት አለዉ፡፡
በማንኛዉም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይቻልም፡፡
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ተወዳዳሪዎች በጨረታዉ አሸናፊ የሆኑና ከተገለጸላቸዉ በአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የዉልማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 5 /አምስት/ ተከታታይ ቀን ድረስ በኮሌጁ ቀርቦ ዉለታ መዉሰድ ይኖርበታል፡፡
እቃዉን እስከ ሃያ በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ተጫራች የቫት የምስክር ወረቀት አብሮ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት በዓል ቀን ከሆነ /ዝግ/ ከሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 46 19 23 60 ወይም 09 12 85 01 04 እና 09 63 51 46 01 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here