ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
127

የጨረታ ቁጥር፤ ባ/ጤ/ሳ/ኮ/ግጨ/ዕግ/01/03/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የባህር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 01 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የተለያዩ የህትመት እቃዎች፣ ሎት 03 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 04 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 05 የተለያዩ የጥገና እቃዎች፣ ሎት 06 የፈርኒቸር እቃ፣ ሎት 07 የተለያዩ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች፣ ሎት 08 የተለያዩ የህክምና መድሃኒቶች እና ሎት 09 የተለያዩ የህክምና ሰፕላይስ እና ኢኩፕመንቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ኮሌጁ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግዥው መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ግልጽ እና ተነባቢ በሆነ መልኩ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከባህር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡
የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እንዲሁም የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ማንኛውንም ግብር ጨምሮ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የሚሞሉትን ጠቅላላ የዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ኦርጅናል የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኮሌጁ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታው ውስጥ አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በአማርኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር ኮሌጁ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኮሌጁ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት ማለትም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 እንዲሁም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 04 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ ባህር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 04 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 07 71 ወይም 058 222 21 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል መግቢያ በር በስተ ምዕራብ ከአማራ ክልል ኦክስጅን ማምረቻ ጎን (ባህር ዳር)

ባህር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here