የጨረታ ቁጥር 004/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ በመደበኛና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 3 ዘይትና ቅባት፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 የመጋረጃ ጨርቅ እና ሎት 6 የውሃ ማጣሪያ ተወዳዳሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የእቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ የሚወዳደሩበትን እቃ ሁለት በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 በ8፡30 ይከፈታል፡፡
የጨረታ መዝጊያ ቀን 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 78/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ