የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
128

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ለማህበሩ ለድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፕሪንተርና ታብሌት) በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በማወዳደር በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን)ያላቸው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘውማቅረብአለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ባህር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘትይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው
የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር / አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here