በአሥራ አንደኛዉ ሰዓት የተገኘዉ

0
121

በፓስፊክ ውቅያኖስ ደቡብ ምእራብ ቀጣና በትልቅነቱ ቀዳሚ ለባህር ውስጥ ፍጥረታት በምግብ እና መጠለያነት የሚያገለግል ተስፋ ሰጪ የደቂቅ ፍጥረታት ስብስብ መገኘቱን ዩፒአይ ድረገጽ በሳይንስ ክፍሉ ለንባብ አብቅቶታል::

ድረ ገጹ ለንባብ እንዳበቃው በመጠኑ ቀዳሚ ነው የተባለለት የደቂቅ ፍጥረታት ስብስብ ባለፈው የጥቅምት ወር በ“ናሽናል ጂኦግራፊ” ኘሮግራም ተመራማሪዎች  ሊገኝ  መቻሉ ለእይታ በቅቷል::

የደቂቅ ፍጥረታት ስብስቡ ከ33 ሜትር በላይ እንደሚረዝም እና ሦስት መቶ ዓመታት ሳያስቆጥር እንደልቀረ ነው ድረ ገጹ ያስነበበው::

በባህር ጠላቂ የምርምር ጀልባ ለእይታ የበቃው ግዙፍ የባህር ህያው የዛጐል ስብስብ ትልቅ ከመሆኑ አንፃር ከህዋ መመልከት መቻሉም በአብነነት ሰፍሯል::

ለዘመናት ያደገው የደቂቅ ፍጥረታት ስብስቡ ደማቅ ወይን ጠጅ፣ ቢጫ፣ ሰማያዊ፣ ቀይ እና ቡናማ ቀለም የተላበሰ ነው::

የዓየር ንብረት ለውጥ አሁን ላይ የብዝሃ ህይወት ውድመት ባስከተለበት እና ህይወት ስጋት ላይ በወደቀበት ዘመን ግዙፉ የፍጥረታት ስብስብ መገኘቱ ትልቅ ብስራት መሆኑ ነው የተሰመረበት- በተመራማሪዎች::

በግኝቱ ላይ አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎችም የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ተቋቁሞ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሳይጠፋ የዘለቀው የባህር ውስጥ ፍጥረታት ስብስብ መገኘት ብሩህ ተስፋን አመላካች መሆኑ ነው የኮራል ሪፍ ዳይሬክተሯ ኤሚሊ ዳርሊግ ያሰመሩበት:: አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎችም በዓየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ተቋቁሞ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሳይጠፋ የዘለቀው የባህር ውስጥ ፍጥረታት ስብስቦች ቢጠበቁ ለመጪው ዘመን ሊተርፉ እና ሊሰፉ የሚችሉ ተፈጥሯዊ ሀብቶች ለመኖራቸው ማሳያ መሆኑን ነው የጠቆሙት::

በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው የዓየር ንብረት ጉባኤም የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሚኖራቸው ተግባራት ተጨማሪ ሀብት መመደብ እንደሚጠበቅበት ነው በማደማደሚያነት የተጠቆመው::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here