በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በመደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ቋሚ እቃ፣ ሎት 5 የተዘጋጅ ልብሶች፣ ሎት 6 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 7 ቆዳ ጫማ እና ሎት 8 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢን ቦድ እስከ 60 /ስልሳ/ ቀን ያላነሰ የሆነ ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ /ሲፒኦ/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉም ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ በድምር አሸናፊ ይሆናል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንድሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ በያንዳንዱ ግዥ ላይ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን የሚያስረክበው በለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 033 114 02 83 /09 14 07 94 81 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በፖስታው ላይ ቀን ፤ ስም ፤ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር የሚወዳደሩበትን ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 20/ ሃያ ብር/ በመክፈል ለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት