ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

ቁጥር 03/2017

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሎት 1 የሰቆጣ ኤፍኤም ራዲዮ ህንጻ እና ፓወር ሃዉስ ግንባታ ሥራ ለማስጨረስ ሎት  2 የሰቆጣ ኤፍኤም የአጥር ሥራ የህንፃ እና የጠቅላላ ተቋራጮችን ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ ብቻ በግልጽ ጨረታ ዘዴ በጋዜጣ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት እና መግዛት ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለግንባታ ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 1 እና 2 ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀን እንዲሁም ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የሰቆጣ አሚኮ ዞን ማስተባበሪያ ቢሮ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የግንባታ ሰነዶችን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡  በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ለሎት 1 እና 2ን በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የህንጻ ግንባታና ፓወር ሃዉስ፣ የአጥር ሥራዉ ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here