አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የህትመት ስራዎች ፣ ሎት 4 ኮምፒተርና ተዛማጅ እና ሎት 5 ፈርኒቸር በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ተጫራቾች የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ስዕቃው በቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በግልጽና በፖስታ በማሸግ የድርጅታቸውን ማዕተም በማሳረፍ ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ገዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 68 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ስዓታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸንው በታሸገ ፖስታ በማድረገ ይህ ማስታቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ15ተኛው ቀን 11፡00 ድረስ ተሸጦ በዚያኑ ቀን 11፡30 ታሽጉ በ16ተኛ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ከጠዋቱ በ3፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው አሸናፊ ላይ ሁለት በመቶ ታከስ የሚቆረጥ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረገና እራሣቸውን ከጨረታው ማግለለ አይችሉም፡፡
- አሽናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት /ምድብ/ ውስጥ የሚገኙትን አቃዎች የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ማስቀጠጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልፃፈ ግን የተሞሉትን ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈስጉ ቢሮ ቁጥር 68 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስክ ቁጥር 058 665 04 83 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት አስር በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ እንደስፈላጊነቱ ከሃያ በመቶ ቀንሶ ወይም ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ማንኛውንም ወጪ ሸፍነው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ሊያደርጉ ነው፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታበቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በአፈፃፀም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
የቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል