ሁለት ክብረወሰኖችን በአንድ ቀን

0
105

የሰርከስ ትራኢት አቅራቢዋ ቻርሎት ሜዝ በገመድ ታስሮ ዓየር ላይ በተንጠለጠለ የብረት ቀለበት ላይ በጀርባዋ እና በክንዶቿ መታጠፊያ ብቻ ተመርኩዛ ረዢም ቆይታ በማሳለፏ በአንድ ቀን ሁለት ክብረወሰን ማስመዝገቧን ዩ ፑ አይ ድረገጽ ለንባብ አብቅቷል፡፡

አውስትራሊያዊዋ የ23 ዓመቷ ቻርሎቲ ሜዝ በክብ ቅርፅ በተሰቀለ ብረት ላይ በመገለባበጥ የተያዘውን የ47 ሴኮንድ የሴቶች ክብረ ወሰን  በማሻሻል ነው አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበችው፡፡

ልምምዷን አጠናቅቃ ክብረወሰን ለማስመዝገብ በባለሙያዎች ፊት ትርኢቷን በአቀረበችበት እለት የተሰማት የቋንጃ መሸማቀቅ ህመም ፈታኝ እንደነበር ያልሸሸገችው ቻርሎት የተንጠለጠለውን ክብ የብረት ቀለበት  በሁለት የእጆችዋ መታጠፊያ ይዛ ለ53 ሰከንዶች በመገለባበጥ የመጀመሪያውን ክብረወሰን ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ከሷ በፊት ከተያዘው 47 ሰከንድ ክብረ ወሰን ስድስት ሰከንድ መብለጧን ልብ ይሏል፡፡

በዚያው እለት እጆችዋን ወደፊት እንዲሁም እግሮቿን ወደ ኋላ ዘርግታ በክብ የብረት ቀለበቱ ላይ በትከሻዋ ተንጠልጥላ በፅናት 63 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመቆየቷ ሁለተኛውን ክብረወሰን ማስመዝገቧም ተገልጿል- በድረገጹ፡፡ በአንድ ቀን ሁለት ክብረወሰን ያስመዘገበችው ወጣት ቻርሎት ስትለማመድ ሞራል የሚሰጣት ሰው ያልነበረ ቢሆንም ለክብረ ወሰን በበቃችበት እለት ግን በርካታ ሰው መገኘቱ እንዳበረታት ጠቁማለች፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here