ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
116

የባህር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባህር ዳር አባይ ማዶ ቀበሌ ህዳር 11 ከኮበል ኢንዱስትሪ ጎን ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ማለትም፡- ሎት 1 ፈርኒቸር፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4 ብረታ ብረት፣ ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 6 የሣይክል መለዋወጫ፣ ሎት 7 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 8 የመኪና ዘይት እና ቅባቶች፣ ሎት 9 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 10 የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 11 ጫማ እና ሎት 12 ብትን ጨርቅ በግልጽ ጨረታ አዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
ተጫራቾች የዋጋዉን ጠቅላላ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በገቢ ደረሰኝ መሂ 1 ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ዋጋቸዉ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋዉን ሀያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡
አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስረከቢያ የዉሉን ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 70.00 /ሰባ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
የእቃዎችን አይነት /ሞዴል/ ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
ጨረታዉ በአየር ላይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ ይሆናል፡፡
ማዕከሉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በተዘረዘረው ጥራት (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82 /058 820 97 84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here