በአፈ/ከሳሽ አስረስ መንግስት በአፈ/ተከሳሾች እነ ደረጃ አድማስ መካከል ባለው ገንዘብ ክርክር ጉዳይ እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ አስባለው መርቀነህ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ክፍት ቦታ በአቶ አዳሙ አሳዩ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሆነው መነሻ ዋጋ 707,811.00 /አባት መቶ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አስራ አንድ/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከታህሳስ 07 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 06 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ አየር ላይ ውሎ ጥር 07 ቀን 2017 ዓ.ም 3፡00 እስከ 6:00 ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት