በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ደም ባንክ አገልግሎት በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የሚውሉ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. ፈርኒቸር እና ሎት 4. ህትመት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ተጫረቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሆኑበትን የምስክር ወረቀት ከሠነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ እና የጨረታ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆኑበትን እቃ እስከ ደም ባንክ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት፡ የመጫኛና የማውረጃ እዲሁም የጉልበት ዋጋ በመሸፈን ማስረከብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ለ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውለታ መውሰድ የሚችሉ፡፡
- ውዱዱሩ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ በሌላ ተጫራች ዋጋ ተንተርሶ መሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው በወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 07/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥን በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ሂደቱ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ፡- ከፈለጉ በመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 033 431 09 93 እና 033 431 26 10 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወልደያ ደም ባንክ