በደቡብ ጐንደር ገንዘብ መምሪያ የታች ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ አገልግሎት ለሚሰጣቸው 1. ለታች ጋይንት ወረዳ ውሃ ጽ/ቤት ኤፍራታ ንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚውል 1ኛ. የሲቪል ሥራ /civil work/ ግንባታ 2ኛ. የማሰራጫ ፣የግፊት መስመር ዝርጋታና የውሃ ማዳያ ግንባታ በGCF በጀት ከደረጃ 5 እና በላይ ለሆኑ ህጋዊ ውሃ ሥራ ተቋራጭ 3ኛ. የኤሌክትሮ መካኒካል መገጣጠሚያ ዕቃዎች ግዥ 4ኛ. የማሽን ኪራይ ኤክስካባተር ግዥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባትና ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ግንባታ በማጓተት ወይም በማዘግየት እገዳ ፣ማስጠንቀቂያ ያልተፃፈበት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃዱን ከአወጡ ጀምሮ ግንባታ ገንብተው የማያውቁ ተቋራጮች ከሆኑ ግብር ከሚከፍሉበት ከወረዳ ላለመሥራታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የግንባታና የአቅርቦት ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የግንባታና የአቅርቦት ዓይነት ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /በመሂ 1/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆኑ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ተሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ በአንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በአካባቢ ጨረታ ከዋለ ጀምሮ በሚቆይ ተከታታይ ለአቅርቦት 15 ቀናት ለግንባታ 21 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለአቅርቦት በ16ኛው ቀን ለግንባታ በ22 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ላይ ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት /በሎት/ በመሆኑ የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላትና ጠቅላላ ድምር ውጤት ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- የተሞላው የጨረታ ሰነድ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ ጉዳዮች ካሉ በግዥ መመሪያው ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ታ/ጋ/ወ/ግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 02 18 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ታች ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት