የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት ሎት1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት3. የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር {ቲን} ያላቸው፤ ግዥው ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ሎት 1. የጽ/መሳሪያ ፣ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ስፔር ፓርት) ፣ሎት 3. የመኪና ጎማ አይነት ዝርዝር መግለ/እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ሌተር ኦፍ ክረዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመሂ1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ዋጋ አንድ በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ በማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅጽ ሞልቶ ማቅብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ስዓት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል በ16ኛው ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዜ ዓመታዊ ውል ስለሚሆን የጨረታውን ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልፅ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በጥቅል ስለሆነ የሙሉ ዕቃ ዋጋ መሞላት አለበት፤ ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና ዕቃዎችን መተማ ወረዳ ንብረት ክፍል በዝርዝር ማሰረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- 9 .በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሰለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583310268 – 0583310047 በመደውል ማግኘት ይችላል፡፡
- አሸናፊው ዕቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሰርዝ ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
11 . በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሰባሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማሰከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም ሲፒኦ በማስያዝ በወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት ፡፡
- የእስቴሽነሪ ጨረታ በተመለከተ ዕቃዉ ወደ ንብረት ክፍል በዝርዝር ገቢ ከመደረጉ በፊት ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን በሚመለከተዉ ባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ወደ ንብረት ክፍል ዕቃዉ ገቢ ማድረግ የሚቻለዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት