ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
106

ለደ/ጎን/ዞን ገንዘብ መምሪያ የቢሮ ግንባታ G+1 ለማስገነባት እና ለደ/ጎን/ዞን ትራንስፖርት ተ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደርበት ጨረታ 140,000.00  /አንድ መቶ አራባ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያት ዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ግንባታ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 12 ከረዳት ገ/ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 22 ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ጎ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በ22ኛዉ ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ፣ እሁድና  የህዝብ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  11. ስለጨረታው ማስተካከያ ከፈለጉ ጨረታው ከመታሸጉ 15 ቀን ቀድሞ ማስተካከያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  12. አሸናፊው በውሉ መሰረት በጥራት ሰርቶ በወቅቱ ካላስረበ በመ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ ወስዶ ውሉን በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  13. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት የዋጋ ድምር አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 07 53 በመደወል ማስረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here